charconvfw/charconv_fw/test/data/ethiopic.ut8
author hgs
Thu, 23 Sep 2010 12:50:02 +0800
changeset 64 f66674566702
parent 0 1fb32624e06b
permissions -rw-r--r--
201033_08

<html>
<head>
  <META HTTP-EQUIV="Content-type: text/{plain,html};Charset=unicode-1-1-utf-8">
  <title>ቴሌኮሚኒኬሽን ወደ ግለሰቦች እጅ ሊገባ ነው የሰሞኑ የሕወሓት አጀንዳ ሆኗል </title>
</head>
<body bgcolor="#fff8dd">

 
<h1 align="center">ቴሌኮሚኒኬሽን ወደ ግለሰቦች እጅ ሊገባ ነው የሰሞኑ የሕወሓት አጀንዳ ሆኗል </h1>

<p>ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ ለሦስተኛ ጊዜ በሚያካሄደው መደበኛ ጉባኤ የፖሊሲ ማሻሻያዎች እርምጃዎች ሊወስድ አቅዷል። ከዚሁ የፖሊሱ ማሻሻያ አንዱ የሆነው ቴሌኮሚኒኬሽንን በግለሰብና በመንግሥት እጅ ሆኖ ሥራውን እንዲቀጥል የሚወስን ነው።</p>

<p>ይህ የፖሊሲ ማሻሻያ እርምጃ በመሥሪያ ቤቱ ሠራተኞችና በሕዝቡ ዘንድ ቅሬታ አስከትሏል። እንደ አንዳንድ ሰዎች አስተያየት ከሆነ ቴሌ በውጪ የግለሰብ ኩባንያዎች እጅ መግባቱ የቴሌኮሚኒኬሽን መሥፋፋትን ያግደዋል። እንደ ኢትዮጵያ ባሉ የቴሌ ስርጭት እጅግ ኋላ ቀር በሆነበት ሀገር በግለሰቦች እጅ ውስጥ መሆኑ በተወሰኑ ቦታዎች ብቻ እንዲያተኩሩና ገጠራማውን የሀገሪቱን ክፍል ችላ ይላሉ። ሲሉ ይደመጣሉ።</p>

<p>የፖሊሲ ማሻሻያው በቴሌ ብቻ ሳይሆን በመከላከያ ኢንዱስትሪዎችና በመብራት ኃይልም ጭምር ለውጪ ኩባንያዎችና ለግለሰቦች ለመስጠት እንደታሰብ ለማወቅ ተችሏል። በተለይ በኃይል ማመንጫ በኩል የኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ መራሹ መንግሥት ሊያተኩርበት እንደሚገባ የሚጠቁሙ ባለሙያዎች አሉ። ለኢንቨስትመንት በራችንን ክፍት የምናደርገው በቂ የኃይል ምንጭ ሲኖር ነው። ያለበለዚያ ያለምንም ኃይል ኢንቨስተርን መጋበዝ በቂ አይደለም። በማለት አንዳንድ ኢንቨስተሮች ያማርራሉ።</p>

<p>በዚሁ የኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ ጉባኤ አስመልክቶ በተሰጠው ሃሳብ በኤርትራና በኢትዮጵያ መሀከል ከተፈጠረው አለመግባባትና ቅሬታ ጠ/ሚኒስትሩ እንዳሉት ሁለቱ ሀገሮች የየራሳቸው የምንዛሪ አካሄድ እንዲኖራቸው በመደረጉ አሉታዊ ተፅእኖ መፈጠሩን አልሸሸጉም። ይህም የሁለቱ ሀገሮች ግንኙነት መሻከርን እንደሚያሳይ ለማወቅ ተችሏል።</p>

<p>በቴሌኮሚኒኬሽን በኩል የተወሰደው እርምጃ እጅግ ያስደነገጣቸው አልጠፉም። ይህንኑ ቅሬታ አስመልክቶ ከመሥሪያ ቤቱ ባልደረቦች መሀከል አነጋግረን በሚቀጥለው ሳምንት ዕትማችን ሪፓርት ይዘን እንቀርባለን።</p>


<p align="center"><a href="/Gazettas/Atkurot/info/Atkurot.utf8.html">ከአገሬ ጥር 1 ቀን 1990</a></p>


</body>
</html>